بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
سَبِّحِ ٱسۡمَ رَبِّكَ ٱلۡأَعۡلَى ١ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ ٱلَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ ٢የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡ وَٱلَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ ٣የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡ وَٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلۡمَرۡعَىٰ ٤የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡ فَجَعَلَهُۥ غُثَآءً أَحۡوَىٰ ٥(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ سَنُقۡرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰٓ ٦(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلۡجَهۡرَ وَمَا يَخۡفَىٰ ٧አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ وَنُيَسِّرُكَ لِلۡيُسۡرَىٰ ٨ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡ فَذَكِّرۡ إِن نَّفَعَتِ ٱلذِّكۡرَىٰ ٩ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡ سَيَذَّكَّرُ مَن يَخۡشَىٰ ١٠(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡ وَيَتَجَنَّبُهَا ٱلۡأَشۡقَى ١١መናጢውም ይርቃታል፡፡ ٱلَّذِي يَصۡلَى ٱلنَّارَ ٱلۡكُبۡرَىٰ ١٢ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡ ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحۡيَىٰ ١٣ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡ قَدۡ أَفۡلَحَ مَن تَزَكَّىٰ ١٤የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ وَذَكَرَ ٱسۡمَ رَبِّهِۦ فَصَلَّىٰ ١٥የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ بَلۡ تُؤۡثِرُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا ١٦ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ وَٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٌ وَأَبۡقَىٰٓ ١٧መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَفِي ٱلصُّحُفِ ٱلۡأُولَىٰ ١٨ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ صُحُفِ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ ١٩በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡