بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ١በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ٢ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٣እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ مَٰلِكِ يَوۡمِ ٱلدِّينِ ٤የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡ إِيَّاكَ نَعۡبُدُ وَإِيَّاكَ نَسۡتَعِينُ ٥አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡ ٱهۡدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ ٦ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِمۡ غَيۡرِ ٱلۡمَغۡضُوبِ عَلَيۡهِمۡ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ ٧የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡
Chapter 1 · 7 verses · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib
Surah Al-Fatihah in Amharic
Tap a verse number for its tafsir
Translation: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.