Millat al-Islam

Chapter 77 · 50 verses · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

Surah Al-Mursalat in Amharic

Arabic with tafsir Listen to Surah Al-Mursalat (1212 reciters)

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلۡمُرۡسَلَٰتِ عُرۡفًا ١ተከታታይ ኾነው በተላኩት፣ فَٱلۡعَٰصِفَٰتِ عَصۡفًا ٢በኀይል መንፈስን ነፋሾች በኾኑትም፣ وَٱلنَّٰشِرَٰتِ نَشۡرًا ٣መበተንን በታኞች በኾኑትም፤ (ነፋሶች)፣ فَٱلۡفَٰرِقَٰتِ فَرۡقًا ٤መለየትን ለይዎች በኾኑትም፣ فَٱلۡمُلۡقِيَٰتِ ذِكۡرًا ٥መገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም፣ عُذۡرًا أَوۡ نُذۡرًا ٦ምክንያትን ለማስወገድ ወይም ለማስፈራራት (ጣይዎች በኾኑት መላእክት) እምላለሁ፡፡ إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَوَٰقِعٌ ٧ያ የምትስፈራሩበት (ትንሣኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው፡፡ فَإِذَا ٱلنُّجُومُ طُمِسَتۡ ٨ከዋክብትም (ብርሃንዋ) በታበሰች ጊዜ፡፡ وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ فُرِجَتۡ ٩ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፡፡ وَإِذَا ٱلۡجِبَالُ نُسِفَتۡ ١٠ጋራዎችም በተንኮተኮቱ ጊዜ፡፡ وَإِذَا ٱلرُّسُلُ أُقِّتَتۡ ١١መልክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፡፡ لِأَيِّ يَوۡمٍ أُجِّلَتۡ ١٢ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ (የሚባል ሲኾን)፤ لِيَوۡمِ ٱلۡفَصۡلِ ١٣ለመለያው ቀን (በተባለ ጊዜ፤ በፍጡሮች መካከል ይፈረዳል)፡፡ وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ ١٤የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ١٥ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ أَلَمۡ نُهۡلِكِ ٱلۡأَوَّلِينَ ١٦የፊተኞቹን (ሕዝቦች) አላጠፋንምን ثُمَّ نُتۡبِعُهُمُ ٱلۡأٓخِرِينَ ١٧ከዚያም የኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን፡፡ كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ ١٨በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ١٩ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ أَلَمۡ نَخۡلُقكُّم مِّن مَّآءٍ مَّهِينٍ ٢٠ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን فَجَعَلۡنَٰهُ فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ ٢١በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በማሕፀን) አደረግነው፡፡ إِلَىٰ قَدَرٍ مَّعۡلُومٍ ٢٢እስከ ታወቀ ልክ ድረስ፡፡ መጠንነውም፤ ምን ያማርንም فَقَدَرۡنَا فَنِعۡمَ ٱلۡقَٰدِرُونَ ٢٣መጣኞች ነን وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٢٤ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ كِفَاتًا ٢٥ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን أَحۡيَآءً وَأَمۡوَٰتًا ٢٦ሕያዋን ኾናችሁ ሙታንም ኾናችሁ፡፡ وَجَعَلۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ شَٰمِخَٰتٍ وَأَسۡقَيۡنَٰكُم مَّآءً فُرَاتًا ٢٧በውስጧም ከፍተኛዎችን ተራራዎች አደረግን፡፡ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٢٨ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ ٱنطَلِقُوٓاْ إِلَىٰ مَا كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ ٢٩«ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት (ቅጣት) አዝግሙ፡፡ ٱنطَلِقُوٓاْ إِلَىٰ ظِلٍّ ذِي ثَلَٰثِ شُعَبٍ ٣٠«ባለ ሦስት ቅርንጫፎች ወደ ኾነው ጥላ አዝግሙ፤» (ይባላሉ)፡፡ لَّا ظَلِيلٍ وَلَا يُغۡنِي مِنَ ٱللَّهَبِ ٣١አጠላይ ያልኾነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ኾነው (አዝግሙ)፡፡ إِنَّهَا تَرۡمِي بِشَرَرٍ كَٱلۡقَصۡرِ ٣٢እርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች፡፡ كَأَنَّهُۥ جِمَٰلَتٌ صُفۡرٌ ٣٣(ቃንቄውም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٣٤ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ هَٰذَا يَوۡمُ لَا يَنطِقُونَ ٣٥ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው፡፡ وَلَا يُؤۡذَنُ لَهُمۡ فَيَعۡتَذِرُونَ ٣٦ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ፤ ለእነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٣٧ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِۖ جَمَعۡنَٰكُمۡ وَٱلۡأَوَّلِينَ ٣٨ይህ መለያው ቀን ነው፡፡ እናንተንም የፊተኞቹንም ሰብሰብናችሁ፡፡ فَإِن كَانَ لَكُمۡ كَيۡدٌ فَكِيدُونِ ٣٩ለናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٤٠ላስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي ظِلَٰلٍ وَعُيُونٍ ٤١ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ وَفَوَٰكِهَ مِمَّا يَشۡتَهُونَ ٤٢ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡ كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ٤٣«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ ٤٤እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٤٥ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ كُلُواْ وَتَمَتَّعُواْ قَلِيلًا إِنَّكُم مُّجۡرِمُونَ ٤٦ብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٤٧ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱرۡكَعُواْ لَا يَرۡكَعُونَ ٤٨«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡ وَيۡلٌ يَوۡمَئِذٍ لِّلۡمُكَذِّبِينَ ٤٩ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَهُۥ يُؤۡمِنُونَ ٥٠ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ

Translation: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.