بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
لَآ أُقۡسِمُ بِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ ١(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡ وَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلنَّفۡسِ ٱللَّوَّامَةِ ٢(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَلَّن نَّجۡمَعَ عِظَامَهُۥ ٣ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን بَلَىٰ قَٰدِرِينَ عَلَىٰٓ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُۥ ٤አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡ بَلۡ يُرِيدُ ٱلۡإِنسَٰنُ لِيَفۡجُرَ أَمَامَهُۥ ٥ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡ يَسۡـَٔلُ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلۡقِيَٰمَةِ ٦«የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡ فَإِذَا بَرِقَ ٱلۡبَصَرُ ٧ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡ وَخَسَفَ ٱلۡقَمَرُ ٨ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡ وَجُمِعَ ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ ٩ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡ يَقُولُ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذٍ أَيۡنَ ٱلۡمَفَرُّ ١٠«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡ كـَلَّا لَا وَزَرَ ١١ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡ إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمُسۡتَقَرُّ ١٢በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ يُنَبَّؤُاْ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذِۭ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ ١٣ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡ بَلِ ٱلۡإِنسَٰنُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦ بَصِيرَةٌ ١٤በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡ وَلَوۡ أَلۡقَىٰ مَعَاذِيرَهُۥ ١٥ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡ لَا تُحَرِّكۡ بِهِۦ لِسَانَكَ لِتَعۡجَلَ بِهِۦٓ ١٦በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡ إِنَّ عَلَيۡنَا جَمۡعَهُۥ وَقُرۡءَانَهُۥ ١٧(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡ فَإِذَا قَرَأۡنَٰهُ فَٱتَّبِعۡ قُرۡءَانَهُۥ ١٨ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡ ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا بَيَانَهُۥ ١٩ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡ كـَلَّا بَلۡ تُحِبُّونَ ٱلۡعَاجِلَةَ ٢٠(ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡ وَتَذَرُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ ٢١መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡ وُجُوهٌ يَوۡمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ ٢٢ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ ٢٣ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ وَوُجُوهٌ يَوۡمَئِذِۭ بَاسِرَةٌ ٢٤ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ تَظُنُّ أَن يُفۡعَلَ بِهَا فَاقِرَةٌ ٢٥በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡ كـَلَّآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلتَّرَاقِيَ ٢٦ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤ وَقِيلَ مَنۡۜ رَاقٍ ٢٧«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡ وَظَنَّ أَنَّهُ ٱلۡفِرَاقُ ٢٨(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡ وَٱلۡتَفَّتِ ٱلسَّاقُ بِٱلسَّاقِ ٢٩ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡ إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمَسَاقُ ٣٠በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡ فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ ٣١አላመነምም አልሰገደምም፡፡ وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ ٣٢ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡ ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ يَتَمَطَّىٰٓ ٣٣ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡ أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰ ٣٤የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡ ثُمَّ أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰٓ ٣٥ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡ أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَن يُتۡرَكَ سُدًى ٣٦ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን أَلَمۡ يَكُ نُطۡفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمۡنَىٰ ٣٧የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ ٣٨ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡ فَجَعَلَ مِنۡهُ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ ٣٩ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡ أَلَيۡسَ ذَٰلِكَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحۡـِۧيَ ٱلۡمَوۡتَىٰ ٤٠ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን