Millat al-Islam

Chapter 53 · 62 verses · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

Surah An-Najm in Amharic

Arabic with tafsir Listen to Surah An-Najm (1285 reciters)
Meccanسورة النجم62 verses

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلنَّجۡمِ إِذَا هَوَىٰ ١በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡ مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمۡ وَمَا غَوَىٰ ٢ነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلۡهَوَىٰٓ ٣ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ إِنۡ هُوَ إِلَّا وَحۡيٌ يُوحَىٰ ٤እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلۡقُوَىٰ ٥ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡ ذُو مِرَّةٍ فَٱسۡتَوَىٰ ٦የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡ وَهُوَ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡأَعۡلَىٰ ٧እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡ ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ ٨ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡ فَكَانَ قَابَ قَوۡسَيۡنِ أَوۡ أَدۡنَىٰ ٩(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡ فَأَوۡحَىٰٓ إِلَىٰ عَبۡدِهِۦ مَآ أَوۡحَىٰ ١٠ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡ مَا كَذَبَ ٱلۡفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ ١١(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ ١٢ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን وَلَقَدۡ رَءَاهُ نَزۡلَةً أُخۡرَىٰ ١٣በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡ عِندَ سِدۡرَةِ ٱلۡمُنتَهَىٰ ١٤በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ عِندَهَا جَنَّةُ ٱلۡمَأۡوَىٰٓ ١٥እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ إِذۡ يَغۡشَى ٱلسِّدۡرَةَ مَا يَغۡشَىٰ ١٦ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ مَا زَاغَ ٱلۡبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ ١٧ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡ لَقَدۡ رَأَىٰ مِنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ ١٨ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡ أَفَرَءَيۡتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلۡعُزَّىٰ ١٩አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ ٢٠ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን) أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلۡأُنثَىٰ ٢١ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን تِلۡكَ إِذًا قِسۡمَةٌ ضِيزَىٰٓ ٢٢ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡ إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٌ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهۡوَى ٱلۡأَنفُسُۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلۡهُدَىٰٓ ٢٣እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡ أَمۡ لِلۡإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ ٢٤ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን فَلِلَّهِ ٱلۡأٓخِرَةُ وَٱلۡأُولَىٰ ٢٥መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ ۞ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ ٢٦በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ لَيُسَمُّونَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ تَسۡمِيَةَ ٱلۡأُنثَىٰ ٢٧እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡ وَمَا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّۖ وَإِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغۡنِي مِنَ ٱلۡحَقِّ شَيۡـًٔا ٢٨ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ فَأَعۡرِضۡ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكۡرِنَا وَلَمۡ يُرِدۡ إِلَّا ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا ٢٩ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡ ذَٰلِكَ مَبۡلَغُهُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱهۡتَدَىٰ ٣٠ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ بِمَا عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ بِٱلۡحُسۡنَى ٣١በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (የጠመመውንና የቀናውን ያውቃል)፡፡ ٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلۡمَغۡفِرَةِۚ هُوَ أَعۡلَمُ بِكُمۡ إِذۡ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَإِذۡ أَنتُمۡ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡۖ فَلَا تُزَكُّوٓاْ أَنفُسَكُمۡۖ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ ٣٢(እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي تَوَلَّىٰ ٣٣ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን وَأَعۡطَىٰ قَلِيلًا وَأَكۡدَىٰٓ ٣٤ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን) أَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلۡغَيۡبِ فَهُوَ يَرَىٰٓ ٣٥የሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን أَمۡ لَمۡ يُنَبَّأۡ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ ٣٦ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን وَإِبۡرَٰهِيمَ ٱلَّذِي وَفَّىٰٓ ٣٧በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን) أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزۡرَ أُخۡرَىٰ ٣٨(እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ وَأَن لَّيۡسَ لِلۡإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ٣٩ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡ وَأَنَّ سَعۡيَهُۥ سَوۡفَ يُرَىٰ ٤٠ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡ ثُمَّ يُجۡزَىٰهُ ٱلۡجَزَآءَ ٱلۡأَوۡفَىٰ ٤١ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡ وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلۡمُنتَهَىٰ ٤٢መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ وَأَنَّهُۥ هُوَ أَضۡحَكَ وَأَبۡكَىٰ ٤٣እነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡ وَأَنَّهُۥ هُوَ أَمَاتَ وَأَحۡيَا ٤٤እነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡ وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰ ٤٥እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡ مِن نُّطۡفَةٍ إِذَا تُمۡنَىٰ ٤٦ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡ وَأَنَّ عَلَيۡهِ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰ ٤٧የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡ وَأَنَّهُۥ هُوَ أَغۡنَىٰ وَأَقۡنَىٰ ٤٨እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡ وَأَنَّهُۥ هُوَ رَبُّ ٱلشِّعۡرَىٰ ٤٩እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡ وَأَنَّهُۥٓ أَهۡلَكَ عَادًا ٱلۡأُولَىٰ ٥٠እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡ وَثَمُودَاْ فَمَآ أَبۡقَىٰ ٥١ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡ وَقَوۡمَ نُوحٍ مِّن قَبۡلُۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ هُمۡ أَظۡلَمَ وَأَطۡغَىٰ ٥٢በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَةَ أَهۡوَىٰ ٥٣የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡ فَغَشَّىٰهَا مَا غَشَّىٰ ٥٤ያለበሳትንም አለበሳት፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ ٥٥ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ هَٰذَا نَذِيرٌ مِّنَ ٱلنُّذُرِ ٱلۡأُولَىٰٓ ٥٦ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡ أَزِفَتِ ٱلۡأٓزِفَةُ ٥٧ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡ لَيۡسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ كَاشِفَةٌ ٥٨ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡ أَفَمِنۡ هَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ تَعۡجَبُونَ ٥٩ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን وَتَضۡحَكُونَ وَلَا تَبۡكُونَ ٦٠ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን وَأَنتُمۡ سَٰمِدُونَ ٦١እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡ فَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ وَٱعۡبُدُواْ ۩ ٦٢ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡

Translation: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.