Millat al-Islam

Chapter 55 · 78 verses · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

Surah Ar-Rahman in Amharic

Arabic with tafsir Listen to Surah Ar-Rahman (1411 reciters)
Medinanسورة الرحمن78 verses

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ٱلرَّحۡمَٰنُ ١አል-ረሕማን፤ عَلَّمَ ٱلۡقُرۡءَانَ ٢ቁርኣንን አስተማረ፡፡ خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ ٣ሰውን ፈጠረ፡፡ عَلَّمَهُ ٱلۡبَيَانَ ٤መናገርን አስተማረው፡፡ ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ بِحُسۡبَانٍ ٥ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡ وَٱلنَّجۡمُ وَٱلشَّجَرُ يَسۡجُدَانِ ٦ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡ وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلۡمِيزَانَ ٧ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ أَلَّا تَطۡغَوۡاْ فِي ٱلۡمِيزَانِ ٨በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡ وَأَقِيمُواْ ٱلۡوَزۡنَ بِٱلۡقِسۡطِ وَلَا تُخۡسِرُواْ ٱلۡمِيزَانَ ٩መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡ وَٱلۡأَرۡضَ وَضَعَهَا لِلۡأَنَامِ ١٠ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡ فِيهَا فَٰكِهَةٌ وَٱلنَّخۡلُ ذَاتُ ٱلۡأَكۡمَامِ ١١በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡ وَٱلۡحَبُّ ذُو ٱلۡعَصۡفِ وَٱلرَّيۡحَانُ ١٢የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ١٣(ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِن صَلۡصَٰلٍ كَٱلۡفَخَّارِ ١٤ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡ وَخَلَقَ ٱلۡجَآنَّ مِن مَّارِجٍ مِّن نَّارٍ ١٥ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ١٦ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ رَبُّ ٱلۡمَشۡرِقَيۡنِ وَرَبُّ ٱلۡمَغۡرِبَيۡنِ ١٧የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ١٨ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ مَرَجَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ يَلۡتَقِيَانِ ١٩ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡ بَيۡنَهُمَا بَرۡزَخٌ لَّا يَبۡغِيَانِ ٢٠(እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٢١ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?› يَخۡرُجُ مِنۡهُمَا ٱللُّؤۡلُؤُ وَٱلۡمَرۡجَانُ ٢٢ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٢٣ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ وَلَهُ ٱلۡجَوَارِ ٱلۡمُنشَـَٔاتُ فِي ٱلۡبَحۡرِ كَٱلۡأَعۡلَٰمِ ٢٤እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٢٥ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ كُلُّ مَنۡ عَلَيۡهَا فَانٍ ٢٦በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ وَيَبۡقَىٰ وَجۡهُ رَبِّكَ ذُو ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ ٢٧የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٢٨ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ يَسۡـَٔلُهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ كُلَّ يَوۡمٍ هُوَ فِي شَأۡنٍ ٢٩በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٣٠ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?› سَنَفۡرُغُ لَكُمۡ أَيُّهَ ٱلثَّقَلَانِ ٣١እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٣٢ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ إِنِ ٱسۡتَطَعۡتُمۡ أَن تَنفُذُواْ مِنۡ أَقۡطَارِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ فَٱنفُذُواْۚ لَا تَنفُذُونَ إِلَّا بِسُلۡطَٰنٍ ٣٣የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም) فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٣٤ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ يُرۡسَلُ عَلَيۡكُمَا شُوَاظٌ مِّن نَّارٍ وَنُحَاسٌ فَلَا تَنتَصِرَانِ ٣٥በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٣٦ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فَإِذَا ٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ وَرۡدَةً كَٱلدِّهَانِ ٣٧ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٣٨ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فَيَوۡمَئِذٍ لَّا يُسۡـَٔلُ عَن ذَنۢبِهِۦٓ إِنسٌ وَلَا جَآنٌّ ٣٩በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٤٠ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ يُعۡرَفُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ بِسِيمَٰهُمۡ فَيُؤۡخَذُ بِٱلنَّوَٰصِي وَٱلۡأَقۡدَامِ ٤١ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٤٢ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡ هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِي يُكَذِّبُ بِهَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ ٤٣ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡ يَطُوفُونَ بَيۡنَهَا وَبَيۡنَ حَمِيمٍ ءَانٍ ٤٤በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٤٥ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ وَلِمَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ جَنَّتَانِ ٤٦በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٤٧ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ ذَوَاتَآ أَفۡنَانٍ ٤٨የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٤٩ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فِيهِمَا عَيۡنَانِ تَجۡرِيَانِ ٥٠በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٥١ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فِيهِمَا مِن كُلِّ فَٰكِهَةٍ زَوۡجَانِ ٥٢በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٥٣ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ فُرُشِۭ بَطَآئِنُهَا مِنۡ إِسۡتَبۡرَقٍۚ وَجَنَى ٱلۡجَنَّتَيۡنِ دَانٍ ٥٤የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٥٥ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فِيهِنَّ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٌ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنٌّ ٥٦በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٥٧ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ كَأَنَّهُنَّ ٱلۡيَاقُوتُ وَٱلۡمَرۡجَانُ ٥٨ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٥٩ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ هَلۡ جَزَآءُ ٱلۡإِحۡسَٰنِ إِلَّا ٱلۡإِحۡسَٰنُ ٦٠የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٦١ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ وَمِن دُونِهِمَا جَنَّتَانِ ٦٢ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٦٣ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?› مُدۡهَآمَّتَانِ ٦٤ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٦٥ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فِيهِمَا عَيۡنَانِ نَضَّاخَتَانِ ٦٦በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٦٧ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فِيهِمَا فَٰكِهَةٌ وَنَخۡلٌ وَرُمَّانٌ ٦٨በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٦٩ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ فِيهِنَّ خَيۡرَٰتٌ حِسَانٌ ٧٠በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٧١ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ حُورٌ مَّقۡصُورَٰتٌ فِي ٱلۡخِيَامِ ٧٢በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٧٣ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٌ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنٌّ ٧٤ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٧٥ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ رَفۡرَفٍ خُضۡرٍ وَعَبۡقَرِيٍّ حِسَانٍ ٧٦በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡ فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ٧٧ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ تَبَٰرَكَ ٱسۡمُ رَبِّكَ ذِي ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ ٧٨የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡

Translation: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.