بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ٱلۡحَآقَّةُ ١እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡ مَا ٱلۡحَآقَّةُ ٢አረጋጋጪቱም (እርሷ) ምንድን ናት وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡحَآقَّةُ ٣አረጋጋጪቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ كَذَّبَتۡ ثَمُودُ وَعَادُۢ بِٱلۡقَارِعَةِ ٤ሰሙድና ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ፡፡ فَأَمَّا ثَمُودُ فَأُهۡلِكُواْ بِٱلطَّاغِيَةِ ٥ሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፋ፤ (ተወደሙ)፡፡ وَأَمَّا عَادٌ فَأُهۡلِكُواْ بِرِيحٍ صَرۡصَرٍ عَاتِيَةٍ ٦ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ፡፡ سَخَّرَهَا عَلَيۡهِمۡ سَبۡعَ لَيَالٍ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومًاۖ فَتَرَى ٱلۡقَوۡمَ فِيهَا صَرۡعَىٰ كَأَنَّهُمۡ أَعۡجَازُ نَخۡلٍ خَاوِيَةٍ ٧ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ ሕዝቦቹንም፤ በውስጧ የተጣሉ ኾነው ልክ ክፍት የኾኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ፡፡ فَهَلۡ تَرَىٰ لَهُم مِّنۢ بَاقِيَةٍ ٨ለእነርሱም ቀሪን ታያለህን وَجَآءَ فِرۡعَوۡنُ وَمَن قَبۡلَهُۥ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَٰتُ بِٱلۡخَاطِئَةِ ٩ፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ፡፡ فَعَصَوۡاْ رَسُولَ رَبِّهِمۡ فَأَخَذَهُمۡ أَخۡذَةً رَّابِيَةً ١٠የጌታቸውንም መልእክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፡፡ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው፡፡ إِنَّا لَمَّا طَغَا ٱلۡمَآءُ حَمَلۡنَٰكُمۡ فِي ٱلۡجَارِيَةِ ١١እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ፡፡ لِنَجۡعَلَهَا لَكُمۡ تَذۡكِرَةً وَتَعِيَهَآ أُذُنٌ وَٰعِيَةٌ ١٢ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የኾነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ፡፡ فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ نَفۡخَةٌ وَٰحِدَةٌ ١٣በቀንዱም አንዲት መንነፋት በተነፋች ጊዜ፡፡ وَحُمِلَتِ ٱلۡأَرۡضُ وَٱلۡجِبَالُ فَدُكَّتَا دَكَّةً وَٰحِدَةً ١٤ምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፡፡ فَيَوۡمَئِذٍ وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ ١٥በዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሣኤ) ትኾናለች፡፡ وَٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَهِيَ يَوۡمَئِذٍ وَاهِيَةٌ ١٦ሰማይም ትቀደዳለች፡፡ ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፡፡ وَٱلۡمَلَكُ عَلَىٰٓ أَرۡجَآئِهَاۚ وَيَحۡمِلُ عَرۡشَ رَبِّكَ فَوۡقَهُمۡ يَوۡمَئِذٍ ثَمَٰنِيَةٌ ١٧መላእክትም በየጫፎችዋ ላይ ይኾናሉ፡፡ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ፡፡ يَوۡمَئِذٍ تُعۡرَضُونَ لَا تَخۡفَىٰ مِنكُمۡ خَافِيَةٌ ١٨በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡ فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ فَيَقُولُ هَآؤُمُ ٱقۡرَءُواْ كِتَٰبِيَهۡ ١٩መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡ إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلَٰقٍ حِسَابِيَهۡ ٢٠«እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡ فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَّاضِيَةٍ ٢١እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ ٢٢በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡ قُطُوفُهَا دَانِيَةٌ ٢٣ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡ كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَآ أَسۡلَفۡتُمۡ فِي ٱلۡأَيَّامِ ٱلۡخَالِيَةِ ٢٤በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡ وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِشِمَالِهِۦ فَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُوتَ كِتَٰبِيَهۡ ٢٥መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡ وَلَمۡ أَدۡرِ مَا حِسَابِيَهۡ ٢٦«ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡ يَٰلَيۡتَهَا كَانَتِ ٱلۡقَاضِيَةَ ٢٧«እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡ مَآ أَغۡنَىٰ عَنِّي مَالِيَهۡۜ ٢٨«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡ هَلَكَ عَنِّي سُلۡطَٰنِيَهۡ ٢٩«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡ خُذُوهُ فَغُلُّوهُ ٣٠«ያዙት፤ እሰሩትም፡፡ ثُمَّ ٱلۡجَحِيمَ صَلُّوهُ ٣١«ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት፡፡ ثُمَّ فِي سِلۡسِلَةٍ ذَرۡعُهَا سَبۡعُونَ ذِرَاعًا فَٱسۡلُكُوهُ ٣٢«ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በኾነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት፡፡» إِنَّهُۥ كَانَ لَا يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ ٱلۡعَظِيمِ ٣٣እርሱ ታላቅ በኾነው አላህ አያምንም ነበርና፡፡ وَلَا يَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِينِ ٣٤ድኾችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና፡፡ فَلَيۡسَ لَهُ ٱلۡيَوۡمَ هَٰهُنَا حَمِيمٌ ٣٥ለእርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም፡፡ وَلَا طَعَامٌ إِلَّا مِنۡ غِسۡلِينٍ ٣٦ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም፡፡ لَّا يَأۡكُلُهُۥٓ إِلَّا ٱلۡخَٰطِـُٔونَ ٣٧ኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ (ይባላል)፡፡ فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَا تُبۡصِرُونَ ٣٨በምታዩትም ነገር እምላለሁ፡፡ وَمَا لَا تُبۡصِرُونَ ٣٩በማታዩትም ነገር፡፡ إِنَّهُۥ لَقَوۡلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ ٤٠እርሱ (ቁርኣን) የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው፡፡ وَمَا هُوَ بِقَوۡلِ شَاعِرٍۚ قَلِيلًا مَّا تُؤۡمِنُونَ ٤١እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ፡፡ وَلَا بِقَوۡلِ كَاهِنٍۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ ٤٢የጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ፡፡ تَنزِيلٌ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ٤٣ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَلَوۡ تَقَوَّلَ عَلَيۡنَا بَعۡضَ ٱلۡأَقَاوِيلِ ٤٤በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤ لَأَخَذۡنَا مِنۡهُ بِٱلۡيَمِينِ ٤٥በኀይል በያዝነው ነበር፡፡ ثُمَّ لَقَطَعۡنَا مِنۡهُ ٱلۡوَتِينَ ٤٦ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡ فَمَا مِنكُم مِّنۡ أَحَدٍ عَنۡهُ حَٰجِزِينَ ٤٧ከእናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም፡፡ وَإِنَّهُۥ لَتَذۡكِرَةٌ لِّلۡمُتَّقِينَ ٤٨እርሱም (ቁርኣን) ለጥንቁቆቹ መገሠጫ ነው፡፡ وَإِنَّا لَنَعۡلَمُ أَنَّ مِنكُم مُّكَذِّبِينَ ٤٩እኛም ከእናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ وَإِنَّهُۥ لَحَسۡرَةٌ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ ٥٠እርሱም (ቁርኣን) በከሓዲዎቹ ላይ ጸጸት ነው፡፡ وَإِنَّهُۥ لَحَقُّ ٱلۡيَقِينِ ٥١እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ ٥٢የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡