بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنفَطَرَتۡ ١ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡكَوَاكِبُ ٱنتَثَرَتۡ ٢ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡبِحَارُ فُجِّرَتۡ ٣ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡقُبُورُ بُعۡثِرَتۡ ٤መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤ عَلِمَتۡ نَفۡسٌ مَّا قَدَّمَتۡ وَأَخَّرَتۡ ٥ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ ٱلۡكَرِيمِ ٦አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ ٱلَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّىٰكَ فَعَدَلَكَ ٧በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ فِيٓ أَيِّ صُورَةٍ مَّا شَآءَ رَكَّبَكَ ٨በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡ كـَلَّا بَلۡ تُكَذِّبُونَ بِٱلدِّينِ ٩ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡ وَإِنَّ عَلَيۡكُمۡ لَحَٰفِظِينَ ١٠በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ كِرَامًا كَٰتِبِينَ ١١የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡ يَعۡلَمُونَ مَا تَفۡعَلُونَ ١٢የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡ إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٍ ١٣እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡ وَإِنَّ ٱلۡفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ ١٤ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡ يَصۡلَوۡنَهَا يَوۡمَ ٱلدِّينِ ١٥በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡ وَمَا هُمۡ عَنۡهَا بِغَآئِبِينَ ١٦እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡ وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ ١٧የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ ثُمَّ مَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ ١٨ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ يَوۡمَ لَا تَمۡلِكُ نَفۡسٌ لِّنَفۡسٍ شَيۡـًٔاۖ وَٱلۡأَمۡرُ يَوۡمَئِذٍ لِّلَّهِ ١٩(እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡