بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمُدَّثِّرُ ١አንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ قُمۡ فَأَنذِرۡ ٢ተነሳ አስጠንቅቅም፡፡ وَرَبَّكَ فَكَبِّرۡ ٣ጌታህንም አክብር፡፡ وَثِيَابَكَ فَطَهِّرۡ ٤ልብስህንም አጥራ፡፡ وَٱلرُّجۡزَ فَٱهۡجُرۡ ٥ጣዖትንም ራቅ፡፡ وَلَا تَمۡنُن تَسۡتَكۡثِرُ ٦ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ፤ (በረከትን) አትለግስለለ وَلِرَبِّكَ فَٱصۡبِرۡ ٧ለጌታህም (ትዕዛዝ) ታገሥ፡፡ فَإِذَا نُقِرَ فِي ٱلنَّاقُورِ ٨በቀንዱም በተነፋ ጊዜ (ነገሩ ይበረታል)፡፡ فَذَٰلِكَ يَوۡمَئِذٍ يَوۡمٌ عَسِيرٌ ٩ይህም (ጊዜ) ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ غَيۡرُ يَسِيرٍ ١٠በከሓዲዎች ላይ ገር ያልኾነ ነው፡፡ ذَرۡنِي وَمَنۡ خَلَقۡتُ وَحِيدًا ١١አንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ وَجَعَلۡتُ لَهُۥ مَالًا مَّمۡدُودًا ١٢ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በያይነቱ) ያደረግሁለት፡፡ وَبَنِينَ شُهُودًا ١٣(በያደባባዩ) ተገኝዎች የኾኑ ወንዶች ልጆችንም፡፡ وَمَهَّدتُّ لَهُۥ تَمۡهِيدًا ١٤ለእርሱም (ኑሮውን) መዘርጋትን የዘረጋሁለት (ከኾነ ሰው ገር ተዎኝ)፡፡ ثُمَّ يَطۡمَعُ أَنۡ أَزِيدَ ١٥ከዚያም ልጨምርለት ይከጅላል፡፡ كـَلَّآۖ إِنَّهُۥ كَانَ لِأٓيَٰتِنَا عَنِيدًا ١٦ይከልከል፤ እርሱ ለአንቀጾቻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበር፡፡ سَأُرۡهِقُهُۥ صَعُودًا ١٧በእርግጥ ችግርን አስገድደዋለሁ፡፡ إِنَّهُۥ فَكَّرَ وَقَدَّرَ ١٨እርሱ (በቁርኣን ነገር) ሐሰበ፤ ገመተም፡፡ فَقُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ ١٩ተረገመም፤ እንዴት ገመተ ثُمَّ قُتِلَ كَيۡفَ قَدَّرَ ٢٠ከዚያም (ከሞት በኋላ) ተረገመ፡፡ እንዴት ገመተ ثُمَّ نَظَرَ ٢١ከዚያም እንደ ገና (በቁርኣኑ ነገር) ተመለከተ፡፡ ثُمَّ عَبَسَ وَبَسَرَ ٢٢ከዚያም ፊቱን አጨፈገገ፤ አኮማተረም፡፡ ثُمَّ أَدۡبَرَ وَٱسۡتَكۡبَرَ ٢٣ከዚያም (ከማመን) ዞረ፤ ኮራም፡፡ فَقَالَ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٌ يُؤۡثَرُ ٢٤አለም «ይህ (ከሌላ) የሚቀዳ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا قَوۡلُ ٱلۡبَشَرِ ٢٥«ይህ የሰው ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፡፡» سَأُصۡلِيهِ سَقَرَ ٢٦በሰቀር ውስጥ በእርግጥ አገባዋለሁ፡፡ وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سَقَرُ ٢٧ሰቀር ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ لَا تُبۡقِي وَلَا تَذَرُ ٢٨(ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም አትተውምም፡፡ لَوَّاحَةٌ لِّلۡبَشَرِ ٢٩ቆዳን በጣም አክሳይ ናት፡፡ عَلَيۡهَا تِسۡعَةَ عَشَرَ ٣٠በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት፡፡ وَمَا جَعَلۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ إِلَّا مَلَٰٓئِكَةًۖ وَمَا جَعَلۡنَا عِدَّتَهُمۡ إِلَّا فِتۡنَةً لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيَسۡتَيۡقِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَيَزۡدَادَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِيمَٰنًا وَلَا يَرۡتَابَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَلِيَقُولَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَٱلۡكَٰفِرُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَمَا يَعۡلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَۚ وَمَا هِيَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡبَشَرِ ٣١የእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፡፡ እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ كـَلَّا وَٱلۡقَمَرِ ٣٢(ከክህደት) ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ፡፡ وَٱلَّيۡلِ إِذۡ أَدۡبَرَ ٣٣በሌሊቱም በኼደ ጊዜ፡፡ وَٱلصُّبۡحِ إِذَآ أَسۡفَرَ ٣٤በንጋቱም ባበራ ጊዜ፡፡ إِنَّهَا لَإِحۡدَى ٱلۡكُبَرِ ٣٥እርሷ (ሰቀር) ከታላላቆቹ (አደጋዎች) አንዷ ናት፡፡ نَذِيرًا لِّلۡبَشَرِ ٣٦ለሰዎች አስፈራሪ ስትኾን፡፡ لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَتَقَدَّمَ أَوۡ يَتَأَخَّرَ ٣٧ከእናንተ (ወደ በጎ ነገር) መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለሻ ሰው (አስፈራሪ ስትኾኑ)፡፡ كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡ رَهِينَةٌ ٣٨ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡ إِلَّآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡيَمِينِ ٣٩የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡ فِي جَنَّٰتٍ يَتَسَآءَلُونَ ٤٠(እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡ عَنِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ ٤١ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡ مَا سَلَكَكُمۡ فِي سَقَرَ ٤٢(ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?» قَالُواْ لَمۡ نَكُ مِنَ ٱلۡمُصَلِّينَ ٤٣(እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡ وَلَمۡ نَكُ نُطۡعِمُ ٱلۡمِسۡكِينَ ٤٤«ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡ وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلۡخَآئِضِينَ ٤٥«ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡ وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ ٤٦«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡ حَتَّىٰٓ أَتَىٰنَا ٱلۡيَقِينُ ٤٧«እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡» فَمَا تَنفَعُهُمۡ شَفَٰعَةُ ٱلشَّٰفِعِينَ ٤٨የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ فَمَا لَهُمۡ عَنِ ٱلتَّذۡكِرَةِ مُعۡرِضِينَ ٤٩ከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው كَأَنَّهُمۡ حُمُرٌ مُّسۡتَنفِرَةٌ ٥٠እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡ فَرَّتۡ مِن قَسۡوَرَةِۭ ٥١ከዐንበሳ የሸሹ፡፡ بَلۡ يُرِيدُ كُلُّ ٱمۡرِيٍٕ مِّنۡهُمۡ أَن يُؤۡتَىٰ صُحُفًا مُّنَشَّرَةً ٥٢ይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡ كـَلَّاۖ بَل لَّا يَخَافُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ ٥٣ይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡ كـَلَّآ إِنَّهُۥ تَذۡكِرَةٌ ٥٤ይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡ فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ ٥٥ስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡ وَمَا يَذۡكُرُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ هُوَ أَهۡلُ ٱلتَّقۡوَىٰ وَأَهۡلُ ٱلۡمَغۡفِرَةِ ٥٦አላህም ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፡፡ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም ባለቤት ነው፡፡