ملة الإسلام

السورة 56 · 96 آية · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

سورة الواقعة باللغة الأمهرية

السورة بالعربية مع التفسير استمع إلى سورة الواقعة (1,362 قارئاً)
مكيةسورة الواقعة٩٦ آية

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

إِذَا وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ ١መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡ لَيۡسَ لِوَقۡعَتِهَا كَاذِبَةٌ ٢ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡ خَافِضَةٌ رَّافِعَةٌ ٣ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡ إِذَا رُجَّتِ ٱلۡأَرۡضُ رَجًّا ٤ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡ وَبُسَّتِ ٱلۡجِبَالُ بَسًّا ٥ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡ فَكَانَتۡ هَبَآءً مُّنۢبَثًّا ٦የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ وَكُنتُمۡ أَزۡوَٰجًا ثَلَٰثَةً ٧ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡ فَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ ٨የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ ٩የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلسَّٰبِقُونَ ١٠(ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡمُقَرَّبُونَ ١١እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ ١٢በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡ ثُلَّةٌ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ ١٣ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ وَقَلِيلٌ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ ١٤ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡ عَلَىٰ سُرُرٍ مَّوۡضُونَةٍ ١٥በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡ مُّتَّكِـِٔينَ عَلَيۡهَا مُتَقَٰبِلِينَ ١٦በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡ يَطُوفُ عَلَيۡهِمۡ وِلۡدَٰنٌ مُّخَلَّدُونَ ١٧በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ بِأَكۡوَابٍ وَأَبَارِيقَ وَكَأۡسٍ مِّن مَّعِينٍ ١٨ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡ لَّا يُصَدَّعُونَ عَنۡهَا وَلَا يُنزِفُونَ ١٩ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡ وَفَٰكِهَةٍ مِّمَّا يَتَخَيَّرُونَ ٢٠ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡ وَلَحۡمِ طَيۡرٍ مِّمَّا يَشۡتَهُونَ ٢١ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡ وَحُورٌ عِينٌ ٢٢ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡ كَأَمۡثَٰلِ ٱللُّؤۡلُوِٕ ٱلۡمَكۡنُونِ ٢٣ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡ جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ٢٤በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡ لَا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوًا وَلَا تَأۡثِيمًا ٢٥በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡ إِلَّا قِيلًا سَلَٰمًا سَلَٰمًا ٢٦ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡ وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ ٢٧የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች فِي سِدۡرٍ مَّخۡضُودٍ ٢٨በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡ وَطَلۡحٍ مَّنضُودٍ ٢٩(ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡ وَظِلٍّ مَّمۡدُودٍ ٣٠በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡ وَمَآءٍ مَّسۡكُوبٍ ٣١በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡ وَفَٰكِهَةٍ كَثِيرَةٍ ٣٢ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡ لَّا مَقۡطُوعَةٍ وَلَا مَمۡنُوعَةٍ ٣٣የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡ وَفُرُشٍ مَّرۡفُوعَةٍ ٣٤ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡ إِنَّآ أَنشَأۡنَٰهُنَّ إِنشَآءً ٣٥እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡ فَجَعَلۡنَٰهُنَّ أَبۡكَارًا ٣٦ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡ عُرُبًا أَتۡرَابًا ٣٧ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡ لِّأَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ ٣٨ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡ ثُلَّةٌ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ ٣٩ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ وَثُلَّةٌ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ ٤٠ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ وَأَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ ٤١የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡ فِي سَمُومٍ وَحَمِيمٍ ٤٢በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡ وَظِلٍّ مِّن يَحۡمُومٍ ٤٣ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡ لَّا بَارِدٍ وَلَا كَرِيمٍ ٤٤ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَبۡلَ ذَٰلِكَ مُتۡرَفِينَ ٤٥እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡ وَكَانُواْ يُصِرُّونَ عَلَى ٱلۡحِنثِ ٱلۡعَظِيمِ ٤٦በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡ وَكَانُواْ يَقُولُونَ أَئِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ ٤٧ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ ٤٨«የፊተኞቹ አባቶቻችንም?» قُلۡ إِنَّ ٱلۡأَوَّلِينَ وَٱلۡأٓخِرِينَ ٤٩በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡ لَمَجۡمُوعُونَ إِلَىٰ مِيقَٰتِ يَوۡمٍ مَّعۡلُومٍ ٥٠«በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡ ثُمَّ إِنَّكُمۡ أَيُّهَا ٱلضَّآلُّونَ ٱلۡمُكَذِّبُونَ ٥١«ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ لَأٓكِلُونَ مِن شَجَرٍ مِّن زَقُّومٍ ٥٢« ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡ فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ ٥٣«ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡ فَشَٰرِبُونَ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡحَمِيمِ ٥٤«በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡ فَشَٰرِبُونَ شُرۡبَ ٱلۡهِيمِ ٥٥«የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡» هَٰذَا نُزُلُهُمۡ يَوۡمَ ٱلدِّينِ ٥٦ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡ نَحۡنُ خَلَقۡنَٰكُمۡ فَلَوۡلَا تُصَدِّقُونَ ٥٧እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን أَفَرَءَيۡتُم مَّا تُمۡنُونَ ٥٨(በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን ءَأَنتُمۡ تَخۡلُقُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡخَٰلِقُونَ ٥٩እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን نَحۡنُ قَدَّرۡنَا بَيۡنَكُمُ ٱلۡمَوۡتَ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ ٦٠እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ أَمۡثَٰلَكُمۡ وَنُنشِئَكُمۡ فِي مَا لَا تَعۡلَمُونَ ٦١ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡ وَلَقَدۡ عَلِمۡتُمُ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُولَىٰ فَلَوۡلَا تَذَكَّرُونَ ٦٢የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን أَفَرَءَيۡتُم مَّا تَحۡرُثُونَ ٦٣የምትዘሩትንም አያችሁን ءَأَنتُمۡ تَزۡرَعُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلزَّٰرِعُونَ ٦٤እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን لَوۡ نَشَآءُ لَجَعَلۡنَٰهُ حُطَٰمًا فَظَلۡتُمۡ تَفَكَّهُونَ ٦٥ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡ إِنَّا لَمُغۡرَمُونَ ٦٦«እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡ بَلۡ نَحۡنُ مَحۡرُومُونَ ٦٧«በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡ أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلۡمَآءَ ٱلَّذِي تَشۡرَبُونَ ٦٨ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን ءَأَنتُمۡ أَنزَلۡتُمُوهُ مِنَ ٱلۡمُزۡنِ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنزِلُونَ ٦٩እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን لَوۡ نَشَآءُ جَعَلۡنَٰهُ أُجَاجًا فَلَوۡلَا تَشۡكُرُونَ ٧٠ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلنَّارَ ٱلَّتِي تُورُونَ ٧١ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን ءَأَنتُمۡ أَنشَأۡتُمۡ شَجَرَتَهَآ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنشِـُٔونَ ٧٢እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን نَحۡنُ جَعَلۡنَٰهَا تَذۡكِرَةً وَمَتَٰعًا لِّلۡمُقۡوِينَ ٧٣እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡ فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ ٧٤የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡ ۞ فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَوَٰقِعِ ٱلنُّجُومِ ٧٥በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡ وَإِنَّهُۥ لَقَسَمٌ لَّوۡ تَعۡلَمُونَ عَظِيمٌ ٧٦እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡ إِنَّهُۥ لَقُرۡءَانٌ كَرِيمٌ ٧٧እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ فِي كِتَٰبٍ مَّكۡنُونٍ ٧٨በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ لَّا يَمَسُّهُۥٓ إِلَّا ٱلۡمُطَهَّرُونَ ٧٩የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡ تَنزِيلٌ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ٨٠ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ أَفَبِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ أَنتُم مُّدۡهِنُونَ ٨١በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን وَتَجۡعَلُونَ رِزۡقَكُمۡ أَنَّكُمۡ تُكَذِّبُونَ ٨٢ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን فَلَوۡلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلۡحُلۡقُومَ ٨٣(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡ وَأَنتُمۡ حِينَئِذٍ تَنظُرُونَ ٨٤እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡ وَنَحۡنُ أَقۡرَبُ إِلَيۡهِ مِنكُمۡ وَلَٰكِن لَّا تُبۡصِرُونَ ٨٥እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡ فَلَوۡلَآ إِن كُنتُمۡ غَيۡرَ مَدِينِينَ ٨٦የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡ تَرۡجِعُونَهَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ٨٧እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡ فَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ ٨٨(ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡ فَرَوۡحٌ وَرَيۡحَانٌ وَجَنَّتُ نَعِيمٍ ٨٩(ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡ وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ ٩٠ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡ فَسَلَٰمٌ لَّكَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ ٩١ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡ وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُكَذِّبِينَ ٱلضَّآلِّينَ ٩٢ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡ فَنُزُلٌ مِّنۡ حَمِيمٍ ٩٣ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡ وَتَصۡلِيَةُ جَحِيمٍ ٩٤በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ حَقُّ ٱلۡيَقِينِ ٩٥ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡ فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ ٩٦የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡

الترجمة: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.