ملة الإسلام

السورة 78 · 40 آية · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

سورة النبأ باللغة الأمهرية

السورة بالعربية مع التفسير استمع إلى سورة النبأ (1,427 قارئاً)
مكيةسورة النبأ٤٠ آية

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

عَمَّ يَتَسَآءَلُونَ ١ከምን ነገር ይጠያየቃሉ عَنِ ٱلنَّبَإِ ٱلۡعَظِيمِ ٢ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡ ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ مُخۡتَلِفُونَ ٣ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡ كـَلَّا سَيَعۡلَمُونَ ٤ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ ثُمَّ كـَلَّا سَيَعۡلَمُونَ ٥ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡ أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ مِهَٰدًا ٦ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادًا ٧ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን وَخَلَقۡنَٰكُمۡ أَزۡوَٰجًا ٨ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَجَعَلۡنَا نَوۡمَكُمۡ سُبَاتًا ٩እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡ وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِبَاسًا ١٠ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡ وَجَعَلۡنَا ٱلنَّهَارَ مَعَاشًا ١١ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡ وَبَنَيۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعًا شِدَادًا ١٢ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡ وَجَعَلۡنَا سِرَاجًا وَهَّاجًا ١٣አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡ وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡمُعۡصِرَٰتِ مَآءً ثَجَّاجًا ١٤ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡ لِّنُخۡرِجَ بِهِۦ حَبًّا وَنَبَاتًا ١٥በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡ وَجَنَّٰتٍ أَلۡفَافًا ١٦የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡ إِنَّ يَوۡمَ ٱلۡفَصۡلِ كَانَ مِيقَٰتًا ١٧የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَتَأۡتُونَ أَفۡوَاجًا ١٨በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡ وَفُتِحَتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ أَبۡوَٰبًا ١٩ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡ وَسُيِّرَتِ ٱلۡجِبَالُ فَكَانَتۡ سَرَابًا ٢٠ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡ إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتۡ مِرۡصَادًا ٢١ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡ لِّلطَّٰغِينَ مَـَٔابًا ٢٢ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡ لَّٰبِثِينَ فِيهَآ أَحۡقَابًا ٢٣በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤ لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرۡدًا وَلَا شَرَابًا ٢٤በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡ إِلَّا حَمِيمًا وَغَسَّاقًا ٢٥ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡ جَزَآءً وِفَاقًا ٢٦ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡ إِنَّهُمۡ كَانُواْ لَا يَرۡجُونَ حِسَابًا ٢٧እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا كِذَّابًا ٢٨በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡ وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ كِتَٰبًا ٢٩ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ فَذُوقُواْ فَلَن نَّزِيدَكُمۡ إِلَّا عَذَابًا ٣٠ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡ إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ مَفَازًا ٣١ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡ حَدَآئِقَ وَأَعۡنَٰبًا ٣٢አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ وَكَوَاعِبَ أَتۡرَابًا ٣٣እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ وَكَأۡسًا دِهَاقًا ٣٤የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡ لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوًا وَلَا كِذَّٰبًا ٣٥በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡ جَزَآءً مِّن رَّبِّكَ عَطَآءً حِسَابًا ٣٦ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡ رَّبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلرَّحۡمَٰنِۖ لَا يَمۡلِكُونَ مِنۡهُ خِطَابًا ٣٧የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡ يَوۡمَ يَقُومُ ٱلرُّوحُ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ صَفًّاۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنۡ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَقَالَ صَوَابًا ٣٨መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ مَـَٔابًا ٣٩ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡ إِنَّآ أَنذَرۡنَٰكُمۡ عَذَابًا قَرِيبًا يَوۡمَ يَنظُرُ ٱلۡمَرۡءُ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُ وَيَقُولُ ٱلۡكَافِرُ يَٰلَيۡتَنِي كُنتُ تُرَٰبَۢا ٤٠እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡

الترجمة: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.