ملة الإسلام

السورة 37 · 182 آية · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

سورة الصافات باللغة الأمهرية

السورة بالعربية مع التفسير استمع إلى سورة الصافات (1,203 قارئاً)
مكيةسورة الصافات١٨٢ آية

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ صَفًّا ١መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ فَٱلزَّٰجِرَٰتِ زَجۡرًا ٢መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ فَٱلتَّٰلِيَٰتِ ذِكۡرًا ٣ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡ إِنَّ إِلَٰهَكُمۡ لَوَٰحِدٌ ٤አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡ رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَرَبُّ ٱلۡمَشَٰرِقِ ٥የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ إِنَّا زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِزِينَةٍ ٱلۡكَوَاكِبِ ٦እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡ وَحِفۡظًا مِّن كُلِّ شَيۡطَٰنٍ مَّارِدٍ ٧አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡ لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى ٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰ وَيُقۡذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٍ ٨ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡ دُحُورًاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ وَاصِبٌ ٩የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡ إِلَّا مَنۡ خَطِفَ ٱلۡخَطۡفَةَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٌ ثَاقِبٌ ١٠ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡ فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَهُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَم مَّنۡ خَلَقۡنَآۚ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّن طِينٍ لَّازِبِۭ ١١ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡ بَلۡ عَجِبۡتَ وَيَسۡخَرُونَ ١٢ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡ وَإِذَا ذُكِّرُواْ لَا يَذۡكُرُونَ ١٣በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡ وَإِذَا رَأَوۡاْ ءَايَةً يَسۡتَسۡخِرُونَ ١٤ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡ وَقَالُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٌ مُّبِينٌ ١٥ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ ١٦«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ ١٧«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡ قُلۡ نَعَمۡ وَأَنتُمۡ دَٰخِرُونَ ١٨«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡ فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٌ وَٰحِدَةٌ فَإِذَا هُمۡ يَنظُرُونَ ١٩እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡ وَقَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا هَٰذَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ ٢٠«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡ هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ ٢١«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡ ۞ ٱحۡشُرُواْ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ وَأَزۡوَٰجَهُمۡ وَمَا كَانُواْ يَعۡبُدُونَ ٢٢(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَٱهۡدُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡجَحِيمِ ٢٣«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡ وَقِفُوهُمۡۖ إِنَّهُم مَّسۡـُٔولُونَ ٢٤«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡ مَا لَكُمۡ لَا تَنَاصَرُونَ ٢٥(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡ بَلۡ هُمُ ٱلۡيَوۡمَ مُسۡتَسۡلِمُونَ ٢٦በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡ وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٍ يَتَسَآءَلُونَ ٢٧የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡ قَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَأۡتُونَنَا عَنِ ٱلۡيَمِينِ ٢٨(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡ قَالُواْ بَل لَّمۡ تَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ ٢٩(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡ وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭۖ بَلۡ كُنتُمۡ قَوۡمًا طَٰغِينَ ٣٠«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡ فَحَقَّ عَلَيۡنَا قَوۡلُ رَبِّنَآۖ إِنَّا لَذَآئِقُونَ ٣١«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡ فَأَغۡوَيۡنَٰكُمۡ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ ٣٢«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡ فَإِنَّهُمۡ يَوۡمَئِذٍ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ ٣٣ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ ٣٤እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ إِنَّهُمۡ كَانُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسۡتَكۡبِرُونَ ٣٥እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡ وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَّجۡنُونِۭ ٣٦እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡ بَلۡ جَآءَ بِٱلۡحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ٣٧አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡ إِنَّكُمۡ لَذَآئِقُواْ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَلِيمِ ٣٨እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡ وَمَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ٣٩ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡ إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ ٤٠ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ رِزۡقٌ مَّعۡلُومٌ ٤١እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡ فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكۡرَمُونَ ٤٢ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤ فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ ٤٣በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡ عَلَىٰ سُرُرٍ مُّتَقَٰبِلِينَ ٤٤ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ يُطَافُ عَلَيۡهِم بِكَأۡسٍ مِّن مَّعِينِۭ ٤٥ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ بَيۡضَآءَ لَذَّةٍ لِّلشَّٰرِبِينَ ٤٦ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡ لَا فِيهَا غَوۡلٌ وَلَا هُمۡ عَنۡهَا يُنزَفُونَ ٤٧በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ عِينٌ ٤٨እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡ كَأَنَّهُنَّ بَيۡضٌ مَّكۡنُونٌ ٤٩እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡ فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٍ يَتَسَآءَلُونَ ٥٠የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡ قَالَ قَآئِلٌ مِّنۡهُمۡ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ ٥١ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ يَقُولُ أَءِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُصَدِّقِينَ ٥٢«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَدِينُونَ ٥٣«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡ قَالَ هَلۡ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ ٥٤እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡ فَٱطَّلَعَ فَرَءَاهُ فِي سَوَآءِ ٱلۡجَحِيمِ ٥٥ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡ قَالَ تَٱللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرۡدِينِ ٥٦ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡ وَلَوۡلَا نِعۡمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ ٱلۡمُحۡضَرِينَ ٥٧«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡» أَفَمَا نَحۡنُ بِمَيِّتِينَ ٥٨(የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን إِلَّا مَوۡتَتَنَا ٱلۡأُولَىٰ وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ ٥٩«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ ٦٠ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ لِمِثۡلِ هَٰذَا فَلۡيَعۡمَلِ ٱلۡعَٰمِلُونَ ٦١ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡ أَذَٰلِكَ خَيۡرٌ نُّزُلًا أَمۡ شَجَرَةُ ٱلزَّقُّومِ ٦٢በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ إِنَّا جَعَلۡنَٰهَا فِتۡنَةً لِّلظَّٰلِمِينَ ٦٣እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡ إِنَّهَا شَجَرَةٌ تَخۡرُجُ فِيٓ أَصۡلِ ٱلۡجَحِيمِ ٦٤እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡ طَلۡعُهَا كَأَنَّهُۥ رُءُوسُ ٱلشَّيَٰطِينِ ٦٥እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡ فَإِنَّهُمۡ لَأٓكِلُونَ مِنۡهَا فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ ٦٦እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡ ثُمَّ إِنَّ لَهُمۡ عَلَيۡهَا لَشَوۡبًا مِّنۡ حَمِيمٍ ٦٧ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡ ثُمَّ إِنَّ مَرۡجِعَهُمۡ لَإِلَى ٱلۡجَحِيمِ ٦٨ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡ إِنَّهُمۡ أَلۡفَوۡاْ ءَابَآءَهُمۡ ضَآلِّينَ ٦٩እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡ فَهُمۡ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمۡ يُهۡرَعُونَ ٧٠እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡ وَلَقَدۡ ضَلَّ قَبۡلَهُمۡ أَكۡثَرُ ٱلۡأَوَّلِينَ ٧١ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡ وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ ٧٢በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُنذَرِينَ ٧٣የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ ٧٤ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ وَلَقَدۡ نَادَىٰنَا نُوحٌ فَلَنِعۡمَ ٱلۡمُجِيبُونَ ٧٥ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን وَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ ٧٦እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡ وَجَعَلۡنَا ذُرِّيَّتَهُۥ هُمُ ٱلۡبَاقِينَ ٧٧ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤ وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ ٧٨በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡ سَلَٰمٌ عَلَىٰ نُوحٍ فِي ٱلۡعَٰلَمِينَ ٧٩«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡» إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ ٨٠እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٨١እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡ ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ ٨٢ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡ ۞ وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِۦ لَإِبۡرَٰهِيمَ ٨٣ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡ إِذۡ جَآءَ رَبَّهُۥ بِقَلۡبٍ سَلِيمٍ ٨٤ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡ إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَاذَا تَعۡبُدُونَ ٨٥«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡ أَئِفۡكًا ءَالِهَةً دُونَ ٱللَّهِ تُرِيدُونَ ٨٦«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ٨٧«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡ فَنَظَرَ نَظۡرَةً فِي ٱلنُّجُومِ ٨٨በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡ فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٌ ٨٩«እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡ فَتَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ مُدۡبِرِينَ ٩٠ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡ فَرَاغَ إِلَىٰٓ ءَالِهَتِهِمۡ فَقَالَ أَلَا تَأۡكُلُونَ ٩١ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?» مَا لَكُمۡ لَا تَنطِقُونَ ٩٢«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?» فَرَاغَ عَلَيۡهِمۡ ضَرۡبَۢا بِٱلۡيَمِينِ ٩٣በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡ فَأَقۡبَلُوٓاْ إِلَيۡهِ يَزِفُّونَ ٩٤ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡ قَالَ أَتَعۡبُدُونَ مَا تَنۡحِتُونَ ٩٥አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?» وَٱللَّهُ خَلَقَكُمۡ وَمَا تَعۡمَلُونَ ٩٦«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡» قَالُواْ ٱبۡنُواْ لَهُۥ بُنۡيَٰنًا فَأَلۡقُوهُ فِي ٱلۡجَحِيمِ ٩٧«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡ فَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدًا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَسۡفَلِينَ ٩٨በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡ وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهۡدِينِ ٩٩አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» رَبِّ هَبۡ لِي مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ ١٠٠ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ فَبَشَّرۡنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ ١٠١ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعۡيَ قَالَ يَٰبُنَيَّ إِنِّيٓ أَرَىٰ فِي ٱلۡمَنَامِ أَنِّيٓ أَذۡبَحُكَ فَٱنظُرۡ مَاذَا تَرَىٰۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفۡعَلۡ مَا تُؤۡمَرُۖ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ ١٠٢ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّآ أَسۡلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلۡجَبِينِ ١٠٣ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ وَنَٰدَيۡنَٰهُ أَن يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ ١٠٤ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ قَدۡ صَدَّقۡتَ ٱلرُّءۡيَآۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ ١٠٥ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡبَلَٰٓؤُاْ ٱلۡمُبِينُ ١٠٦ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ وَفَدَيۡنَٰهُ بِذِبۡحٍ عَظِيمٍ ١٠٧በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡ وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ ١٠٨በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡ سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ ١٠٩ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ ١١٠እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ١١١እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ وَبَشَّرۡنَٰهُ بِإِسۡحَٰقَ نَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ ١١٢በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ وَبَٰرَكۡنَا عَلَيۡهِ وَعَلَىٰٓ إِسۡحَٰقَۚ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحۡسِنٌ وَظَالِمٌ لِّنَفۡسِهِۦ مُبِينٌ ١١٣በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡ وَلَقَدۡ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ١١٤በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡ وَنَجَّيۡنَٰهُمَا وَقَوۡمَهُمَا مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ ١١٥እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡ وَنَصَرۡنَٰهُمۡ فَكَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ ١١٦ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ وَءَاتَيۡنَٰهُمَا ٱلۡكِتَٰبَ ٱلۡمُسۡتَبِينَ ١١٧በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡ وَهَدَيۡنَٰهُمَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ ١١٨ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡ وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِمَا فِي ٱلۡأٓخِرِينَ ١١٩በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡ سَلَٰمٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ١٢٠ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ ١٢١እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ إِنَّهُمَا مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ١٢٢ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡ وَإِنَّ إِلۡيَاسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ١٢٣ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَلَا تَتَّقُونَ ١٢٤ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን أَتَدۡعُونَ بَعۡلًا وَتَذَرُونَ أَحۡسَنَ ٱلۡخَٰلِقِينَ ١٢٥በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን ٱللَّهَ رَبَّكُمۡ وَرَبَّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ ١٢٦አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን) فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ ١٢٧አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡ إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ ١٢٨ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ ١٢٩በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡ سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِلۡ يَاسِينَ ١٣٠ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ ١٣١እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ١٣٢እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡ وَإِنَّ لُوطًا لَّمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ١٣٣ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ إِذۡ نَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ ١٣٤እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ إِلَّا عَجُوزًا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ ١٣٥(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡ ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ ١٣٦ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡ وَإِنَّكُمۡ لَتَمُرُّونَ عَلَيۡهِم مُّصۡبِحِينَ ١٣٧እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡ وَبِٱلَّيۡلِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ١٣٨በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ١٣٩ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ إِذۡ أَبَقَ إِلَى ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ ١٤٠ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُدۡحَضِينَ ١٤١ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡ فَٱلۡتَقَمَهُ ٱلۡحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ ١٤٢እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡ فَلَوۡلَآ أَنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلۡمُسَبِّحِينَ ١٤٣እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤ لَلَبِثَ فِي بَطۡنِهِۦٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ ١٤٤እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡ ۞ فَنَبَذۡنَٰهُ بِٱلۡعَرَآءِ وَهُوَ سَقِيمٌ ١٤٥እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡ وَأَنۢبَتۡنَا عَلَيۡهِ شَجَرَةً مِّن يَقۡطِينٍ ١٤٦በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡ وَأَرۡسَلۡنَٰهُ إِلَىٰ مِاْئَةِ أَلۡفٍ أَوۡ يَزِيدُونَ ١٤٧ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡ فَـَٔامَنُواْ فَمَتَّعۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ حِينٍ ١٤٨አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡ فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَلِرَبِّكَ ٱلۡبَنَاتُ وَلَهُمُ ٱلۡبَنُونَ ١٤٩(የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?» أَمۡ خَلَقۡنَا ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ إِنَٰثًا وَهُمۡ شَٰهِدُونَ ١٥٠ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን أَلَآ إِنَّهُم مِّنۡ إِفۡكِهِمۡ لَيَقُولُونَ ١٥١ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡ وَلَدَ ٱللَّهُ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ ١٥٢«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ أَصۡطَفَى ٱلۡبَنَاتِ عَلَى ٱلۡبَنِينَ ١٥٣በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ ١٥٤ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ١٥٥አትገነዘቡምን أَمۡ لَكُمۡ سُلۡطَٰنٌ مُّبِينٌ ١٥٦ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን فَأۡتُواْ بِكِتَٰبِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ١٥٧«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡ وَجَعَلُواْ بَيۡنَهُۥ وَبَيۡنَ ٱلۡجِنَّةِ نَسَبًاۚ وَلَقَدۡ عَلِمَتِ ٱلۡجِنَّةُ إِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ ١٥٨በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ ١٥٩አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡ إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ ١٦٠ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡ فَإِنَّكُمۡ وَمَا تَعۡبُدُونَ ١٦١እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤ مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ بِفَٰتِنِينَ ١٦٢በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡ إِلَّا مَنۡ هُوَ صَالِ ٱلۡجَحِيمِ ١٦٣ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡ وَمَا مِنَّآ إِلَّا لَهُۥ مَقَامٌ مَّعۡلُومٌ ١٦٤(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡ وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلصَّآفُّونَ ١٦٥እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡ وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡمُسَبِّحُونَ ١٦٦እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡ وَإِن كَانُواْ لَيَقُولُونَ ١٦٧እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡ لَوۡ أَنَّ عِندَنَا ذِكۡرًا مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ ١٦٨«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤ لَكُنَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ ١٦٩«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡» فَكَفَرُواْ بِهِۦۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ ١٧٠ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ وَلَقَدۡ سَبَقَتۡ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا ٱلۡمُرۡسَلِينَ ١٧١(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡ إِنَّهُمۡ لَهُمُ ٱلۡمَنصُورُونَ ١٧٢እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ ١٧٣ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٍ ١٧٤ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡ وَأَبۡصِرۡهُمۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ ١٧٥እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡ أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ ١٧٦በቅጣታችንም ያቻኩላሉን فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمۡ فَسَآءَ صَبَاحُ ٱلۡمُنذَرِينَ ١٧٧በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ وَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٍ ١٧٨እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡ وَأَبۡصِرۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ ١٧٩ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡ سُبۡحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلۡعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ ١٨٠የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلۡمُرۡسَلِينَ ١٨١በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤ وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ١٨٢ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡

الترجمة: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.