ملة الإسلام

السورة 86 · 17 آية · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

سورة الطارق باللغة الأمهرية

السورة بالعربية مع التفسير استمع إلى سورة الطارق (1,326 قارئاً)
مكيةسورة الطارق١٧ آية

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلسَّمَآءِ وَٱلطَّارِقِ ١በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡ وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلطَّارِقُ ٢የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ ٱلنَّجۡمُ ٱلثَّاقِبُ ٣ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡ إِن كُلُّ نَفۡسٍ لَّمَّا عَلَيۡهَا حَافِظٌ ٤ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ مِمَّ خُلِقَ ٥ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ خُلِقَ مِن مَّآءٍ دَافِقٍ ٦ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ يَخۡرُجُ مِنۢ بَيۡنِ ٱلصُّلۡبِ وَٱلتَّرَآئِبِ ٧ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡ إِنَّهُۥ عَلَىٰ رَجۡعِهِۦ لَقَادِرٌ ٨እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡ يَوۡمَ تُبۡلَى ٱلسَّرَآئِرُ ٩ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡ فَمَا لَهُۥ مِن قُوَّةٍ وَلَا نَاصِرٍ ١٠ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡ وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلرَّجۡعِ ١١የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡ وَٱلۡأَرۡضِ ذَاتِ ٱلصَّدۡعِ ١٢(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤ إِنَّهُۥ لَقَوۡلٌ فَصۡلٌ ١٣እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡ وَمَا هُوَ بِٱلۡهَزۡلِ ١٤እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡ إِنَّهُمۡ يَكِيدُونَ كَيۡدًا ١٥እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ وَأَكِيدُ كَيۡدًا ١٦(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡ فَمَهِّلِ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَمۡهِلۡهُمۡ رُوَيۡدَۢا ١٧ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡

الترجمة: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.