Millat al-Islam

Chapter 84 · 25 verses · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

Surah Al-Inshiqaq in Amharic

Arabic with tafsir Listen to Surah Al-Inshiqaq (1262 reciters)

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنشَقَّتۡ ١ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤ وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ ٢ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤ وَإِذَا ٱلۡأَرۡضُ مُدَّتۡ ٣ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤ وَأَلۡقَتۡ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتۡ ٤በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤ وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ ٥ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدۡحًا فَمُلَٰقِيهِ ٦አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡ فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ ٧መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤ فَسَوۡفَ يُحَاسَبُ حِسَابًا يَسِيرًا ٨በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡ وَيَنقَلِبُ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورًا ٩ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡ وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ وَرَآءَ ظَهۡرِهِۦ ١٠መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤ فَسَوۡفَ يَدۡعُواْ ثُبُورًا ١١(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡ وَيَصۡلَىٰ سَعِيرًا ١٢የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡ إِنَّهُۥ كَانَ فِيٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورًا ١٣እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡ إِنَّهُۥ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ ١٤እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡ بَلَىٰٓۚ إِنَّ رَبَّهُۥ كَانَ بِهِۦ بَصِيرًا ١٥አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡ فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلشَّفَقِ ١٦አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡ وَٱلَّيۡلِ وَمَا وَسَقَ ١٧በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤ وَٱلۡقَمَرِ إِذَا ٱتَّسَقَ ١٨በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡ لَتَرۡكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٍ ١٩ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡ فَمَا لَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ ٢٠የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው وَإِذَا قُرِئَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقُرۡءَانُ لَا يَسۡجُدُونَۤ ۩ ٢١በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው) بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُكَذِّبُونَ ٢٢በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُوعُونَ ٢٣አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡ فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ ٢٤በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡ إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونِۭ ٢٥ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡

Translation: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.