Millat al-Islam

Chapter 92 · 21 verses · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

Surah Al-Lail in Amharic

Arabic with tafsir Listen to Surah Al-Lail (1283 reciters)
Meccanسورة الليل21 verses

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَغۡشَىٰ ١በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡ وَٱلنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ ٢በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡ وَمَا خَلَقَ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ ٣ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡ إِنَّ سَعۡيَكُمۡ لَشَتَّىٰ ٤ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡ فَأَمَّا مَنۡ أَعۡطَىٰ وَٱتَّقَىٰ ٥የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡ وَصَدَّقَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ ٦በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤ فَسَنُيَسِّرُهُۥ لِلۡيُسۡرَىٰ ٧ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ وَأَمَّا مَنۢ بَخِلَ وَٱسۡتَغۡنَىٰ ٨የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤ وَكَذَّبَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ ٩በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤ فَسَنُيَسِّرُهُۥ لِلۡعُسۡرَىٰ ١٠ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ وَمَا يُغۡنِي عَنۡهُ مَالُهُۥٓ إِذَا تَرَدَّىٰٓ ١١በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡ إِنَّ عَلَيۡنَا لَلۡهُدَىٰ ١٢ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡ وَإِنَّ لَنَا لَلۡأٓخِرَةَ وَٱلۡأُولَىٰ ١٣መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡ فَأَنذَرۡتُكُمۡ نَارًا تَلَظَّىٰ ١٤የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡ لَا يَصۡلَىٰهَآ إِلَّا ٱلۡأَشۡقَى ١٥ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡ ٱلَّذِي كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ ١٦ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡ وَسَيُجَنَّبُهَا ٱلۡأَتۡقَى ١٧አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡ ٱلَّذِي يُؤۡتِي مَالَهُۥ يَتَزَكَّىٰ ١٨ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡ وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُۥ مِن نِّعۡمَةٍ تُجۡزَىٰٓ ١٩ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡ إِلَّا ٱبۡتِغَآءَ وَجۡهِ رَبِّهِ ٱلۡأَعۡلَىٰ ٢٠ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡ وَلَسَوۡفَ يَرۡضَىٰ ٢١ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡

Translation: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.