بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
إِذَا ٱلشَّمۡسُ كُوِّرَتۡ ١ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلنُّجُومُ ٱنكَدَرَتۡ ٢ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡجِبَالُ سُيِّرَتۡ ٣ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡعِشَارُ عُطِّلَتۡ ٤የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡوُحُوشُ حُشِرَتۡ ٥እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡبِحَارُ سُجِّرَتۡ ٦ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلنُّفُوسُ زُوِّجَتۡ ٧ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡمَوۡءُۥدَةُ سُئِلَتۡ ٨በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤ بِأَيِّ ذَنۢبٍ قُتِلَتۡ ٩በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤ وَإِذَا ٱلصُّحُفُ نُشِرَتۡ ١٠ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ كُشِطَتۡ ١١ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡجَحِيمُ سُعِّرَتۡ ١٢ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤ وَإِذَا ٱلۡجَنَّةُ أُزۡلِفَتۡ ١٣ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤ عَلِمَتۡ نَفۡسٌ مَّآ أَحۡضَرَتۡ ١٤ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤ فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلۡخُنَّسِ ١٥ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡ ٱلۡجَوَارِ ٱلۡكُنَّسِ ١٦ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡ وَٱلَّيۡلِ إِذَا عَسۡعَسَ ١٧በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤ وَٱلصُّبۡحِ إِذَا تَنَفَّسَ ١٨በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡ إِنَّهُۥ لَقَوۡلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ ١٩እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡ ذِي قُوَّةٍ عِندَ ذِي ٱلۡعَرۡشِ مَكِينٍ ٢٠የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡ مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ ٢١በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجۡنُونٍ ٢٢ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ وَلَقَدۡ رَءَاهُ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡمُبِينِ ٢٣በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡ وَمَا هُوَ عَلَى ٱلۡغَيۡبِ بِضَنِينٍ ٢٤እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ بِقَوۡلِ شَيۡطَٰنٍ رَّجِيمٍ ٢٥እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡ فَأَيۡنَ تَذۡهَبُونَ ٢٦ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٌ لِّلۡعَٰلَمِينَ ٢٧እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَسۡتَقِيمَ ٢٨ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡ وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ٢٩የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡