Millat al-Islam

Chapter 80 · 42 verses · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

Surah Abasa in Amharic

Arabic with tafsir Listen to Surah Abasa (1306 reciters)
Meccanسورة عبس42 verses

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

عَبَسَ وَتَوَلَّىٰٓ ١ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ أَن جَآءَهُ ٱلۡأَعۡمَىٰ ٢ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّهُۥ يَزَّكَّىٰٓ ٣ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ أَوۡ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ ٱلذِّكۡرَىٰٓ ٤ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡ أَمَّا مَنِ ٱسۡتَغۡنَىٰ ٥የተብቃቃው ሰውማ፤ فَأَنتَ لَهُۥ تَصَدَّىٰ ٦አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡ وَمَا عَلَيۡكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ ٧ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡ وَأَمَّا مَن جَآءَكَ يَسۡعَىٰ ٨እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤ وَهُوَ يَخۡشَىٰ ٩እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ فَأَنتَ عَنۡهُ تَلَهَّىٰ ١٠አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡ كـَلَّآ إِنَّهَا تَذۡكِرَةٌ ١١ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡ فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ ١٢የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡ فِي صُحُفٍ مُّكَرَّمَةٍ ١٣በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡ مَّرۡفُوعَةٍ مُّطَهَّرَةِۭ ١٤ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡ بِأَيۡدِي سَفَرَةٍ ١٥በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ كِرَامِۭ بَرَرَةٍ ١٦የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡ قُتِلَ ٱلۡإِنسَٰنُ مَآ أَكۡفَرَهُۥ ١٧ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው مِنۡ أَيِّ شَيۡءٍ خَلَقَهُۥ ١٨(ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን) مِن نُّطۡفَةٍ خَلَقَهُۥ فَقَدَّرَهُۥ ١٩ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡ ثُمَّ ٱلسَّبِيلَ يَسَّرَهُۥ ٢٠ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡ ثُمَّ أَمَاتَهُۥ فَأَقۡبَرَهُۥ ٢١ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡ ثُمَّ إِذَا شَآءَ أَنشَرَهُۥ ٢٢ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡ كـَلَّا لَمَّا يَقۡضِ مَآ أَمَرَهُۥ ٢٣በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡ فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ إِلَىٰ طَعَامِهِۦٓ ٢٤ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡ أَنَّا صَبَبۡنَا ٱلۡمَآءَ صَبًّا ٢٥እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡ ثُمَّ شَقَقۡنَا ٱلۡأَرۡضَ شَقًّا ٢٦ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ فَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا حَبًّا ٢٧በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ وَعِنَبًا وَقَضۡبًا ٢٨ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤ وَزَيۡتُونًا وَنَخۡلًا ٢٩የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ وَحَدَآئِقَ غُلۡبًا ٣٠ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ وَفَٰكِهَةً وَأَبًّا ٣١ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡ مَّتَٰعًا لَّكُمۡ وَلِأَنۡعَٰمِكُمۡ ٣٢ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ فَإِذَا جَآءَتِ ٱلصَّآخَّةُ ٣٣አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ يَوۡمَ يَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِيهِ ٣٤ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ وَأُمِّهِۦ وَأَبِيهِ ٣٥ከናቱም ካባቱም፤ وَصَٰحِبَتِهِۦ وَبَنِيهِ ٣٦ከሚስቱም ከልጁም፤ لِكُلِّ ٱمۡرِيٍٕ مِّنۡهُمۡ يَوۡمَئِذٍ شَأۡنٌ يُغۡنِيهِ ٣٧ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡ وُجُوهٌ يَوۡمَئِذٍ مُّسۡفِرَةٌ ٣٨ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ ضَاحِكَةٌ مُّسۡتَبۡشِرَةٌ ٣٩ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡ وَوُجُوهٌ يَوۡمَئِذٍ عَلَيۡهَا غَبَرَةٌ ٤٠ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤ تَرۡهَقُهَا قَتَرَةٌ ٤١ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَفَرَةُ ٱلۡفَجَرَةُ ٤٢እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡

Translation: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.