ملة الإسلام

السورة 90 · 20 آية · Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib

سورة البلد باللغة الأمهرية

السورة بالعربية مع التفسير استمع إلى سورة البلد (1,326 قارئاً)
مكيةسورة البلد٢٠ آية

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

لَآ أُقۡسِمُ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ ١በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ وَأَنتَ حِلُّۢ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ ٢አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ ٣በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِي كَبَدٍ ٤ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ أَيَحۡسَبُ أَن لَّن يَقۡدِرَ عَلَيۡهِ أَحَدٌ ٥በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን يَقُولُ أَهۡلَكۡتُ مَالًا لُّبَدًا ٦«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ أَيَحۡسَبُ أَن لَّمۡ يَرَهُۥٓ أَحَدٌ ٧አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን أَلَمۡ نَجۡعَل لَّهُۥ عَيۡنَيۡنِ ٨ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን وَلِسَانًا وَشَفَتَيۡنِ ٩ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ وَهَدَيۡنَٰهُ ٱلنَّجۡدَيۡنِ ١٠ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን فَلَا ٱقۡتَحَمَ ٱلۡعَقَبَةَ ١١ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡعَقَبَةُ ١٢ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ فَكُّ رَقَبَةٍ ١٣(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ أَوۡ إِطۡعَٰمٌ فِي يَوۡمٍ ذِي مَسۡغَبَةٍ ١٤ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ يَتِيمًا ذَا مَقۡرَبَةٍ ١٥የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ أَوۡ مِسۡكِينًا ذَا مَتۡرَبَةٍ ١٦ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ ثُمَّ كَانَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡمَرۡحَمَةِ ١٧(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ ١٨እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ ١٩እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ عَلَيۡهِمۡ نَارٌ مُّؤۡصَدَةُۢ ٢٠በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡

الترجمة: Muhammed Sadiq And Muhammed Sani Habib.