بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلۡفَجۡرِ ١በጎህ እምላለሁ፡፡ وَلَيَالٍ عَشۡرٍ ٢በዐሥር ሌሊቶችም፡፡ وَٱلشَّفۡعِ وَٱلۡوَتۡرِ ٣በጥንዱም በነጠላውም፡፡ وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَسۡرِ ٤በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡ هَلۡ فِي ذَٰلِكَ قَسَمٌ لِّذِي حِجۡرٍ ٥በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን أَلَمۡ تَرَ كَيۡفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ ٦ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን إِرَمَ ذَاتِ ٱلۡعِمَادِ ٧በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡ ٱلَّتِي لَمۡ يُخۡلَقۡ مِثۡلُهَا فِي ٱلۡبِلَٰدِ ٨በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡ وَثَمُودَ ٱلَّذِينَ جَابُواْ ٱلصَّخۡرَ بِٱلۡوَادِ ٩በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡ وَفِرۡعَوۡنَ ذِي ٱلۡأَوۡتَادِ ١٠በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡ ٱلَّذِينَ طَغَوۡاْ فِي ٱلۡبِلَٰدِ ١١በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡ فَأَكۡثَرُواْ فِيهَا ٱلۡفَسَادَ ١٢በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን) فَصَبَّ عَلَيۡهِمۡ رَبُّكَ سَوۡطَ عَذَابٍ ١٣በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡ إِنَّ رَبَّكَ لَبِٱلۡمِرۡصَادِ ١٤ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡ فَأَمَّا ٱلۡإِنسَٰنُ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ رَبُّهُۥ فَأَكۡرَمَهُۥ وَنَعَّمَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَكۡرَمَنِ ١٥ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡ وَأَمَّآ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ فَقَدَرَ عَلَيۡهِ رِزۡقَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَهَٰنَنِ ١٦በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡ كـَلَّاۖ بَل لَّا تُكۡرِمُونَ ٱلۡيَتِيمَ ١٧ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡ وَلَا تَحَٰٓضُّونَ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِينِ ١٨ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡ وَتَأۡكُلُونَ ٱلتُّرَاثَ أَكۡلًا لَّمًّا ١٩የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡ وَتُحِبُّونَ ٱلۡمَالَ حُبًّا جَمًّا ٢٠ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡ كـَلَّآۖ إِذَا دُكَّتِ ٱلۡأَرۡضُ دَكًّا دَكًّا ٢١ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤ وَجَآءَ رَبُّكَ وَٱلۡمَلَكُ صَفًّا صَفًّا ٢٢መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ፤ وَجِاْيٓءَ يَوۡمَئِذِۭ بِجَهَنَّمَۚ يَوۡمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ ٱلۡإِنسَٰنُ وَأَنَّىٰ لَهُ ٱلذِّكۡرَىٰ ٢٣ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ يَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي قَدَّمۡتُ لِحَيَاتِي ٢٤«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡ فَيَوۡمَئِذٍ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُۥٓ أَحَدٌ ٢٥በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡ وَلَا يُوثِقُ وَثَاقَهُۥٓ أَحَدٌ ٢٦የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡ يَٰٓأَيَّتُهَا ٱلنَّفۡسُ ٱلۡمُطۡمَئِنَّةُ ٢٧(ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ ٱرۡجِعِيٓ إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرۡضِيَّةً ٢٨«ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡ فَٱدۡخُلِي فِي عِبَٰدِي ٢٩«በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡ وَٱدۡخُلِي جَنَّتِي ٣٠ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡