بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡغَٰشِيَةِ ١የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን وُجُوهٌ يَوۡمَئِذٍ خَٰشِعَةٌ ٢ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡ عَامِلَةٌ نَّاصِبَةٌ ٣ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡ تَصۡلَىٰ نَارًا حَامِيَةً ٤ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡ تُسۡقَىٰ مِنۡ عَيۡنٍ ءَانِيَةٍ ٥በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡ لَّيۡسَ لَهُمۡ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٍ ٦ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡ لَّا يُسۡمِنُ وَلَا يُغۡنِي مِن جُوعٍ ٧የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡ وُجُوهٌ يَوۡمَئِذٍ نَّاعِمَةٌ ٨ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡ لِّسَعۡيِهَا رَاضِيَةٌ ٩ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ ١٠በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡ لَّا تَسۡمَعُ فِيهَا لَٰغِيَةً ١١በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡ فِيهَا عَيۡنٌ جَارِيَةٌ ١٢በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡ فِيهَا سُرُرٌ مَّرۡفُوعَةٌ ١٣በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡ وَأَكۡوَابٌ مَّوۡضُوعَةٌ ١٤በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡ وَنَمَارِقُ مَصۡفُوفَةٌ ١٥የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡ وَزَرَابِيُّ مَبۡثُوثَةٌ ١٦የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡ أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى ٱلۡإِبِلِ كَيۡفَ خُلِقَتۡ ١٧(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች وَإِلَى ٱلسَّمَآءِ كَيۡفَ رُفِعَتۡ ١٨ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች وَإِلَى ٱلۡجِبَالِ كَيۡفَ نُصِبَتۡ ١٩ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ وَإِلَى ٱلۡأَرۡضِ كَيۡفَ سُطِحَتۡ ٢٠ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን) فَذَكِّرۡ إِنَّمَآ أَنتَ مُذَكِّرٌ ٢١አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡ لَّسۡتَ عَلَيۡهِم بِمُصَيۡطِرٍ ٢٢በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡ إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ ٢٣ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤ فَيُعَذِّبُهُ ٱللَّهُ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَكۡبَرَ ٢٤አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡ إِنَّ إِلَيۡنَآ إِيَابَهُمۡ ٢٥መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡ ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا حِسَابَهُم ٢٦ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡