بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِي خَلَقَ ١አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِنۡ عَلَقٍ ٢ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ ٣አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ ٱلَّذِي عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ ٤ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ عَلَّمَ ٱلۡإِنسَٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ ٥ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ كـَلَّآ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَيَطۡغَىٰٓ ٦በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ أَن رَّءَاهُ ٱسۡتَغۡنَىٰٓ ٧ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجۡعَىٰٓ ٨መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ أَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي يَنۡهَىٰ ٩አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰٓ ١٠ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ أَرَءَيۡتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلۡهُدَىٰٓ ١١አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ أَوۡ أَمَرَ بِٱلتَّقۡوَىٰٓ ١٢ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ أَرَءَيۡتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ ١٣አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ أَلَمۡ يَعۡلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ ١٤አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን كـَلَّا لَئِن لَّمۡ يَنتَهِ لَنَسۡفَعَۢا بِٱلنَّاصِيَةِ ١٥ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ نَاصِيَةٍ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٍ ١٦ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ فَلۡيَدۡعُ نَادِيَهُۥ ١٧ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ سَنَدۡعُ ٱلزَّبَانِيَةَ ١٨(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ كـَلَّا لَا تُطِعۡهُ وَٱسۡجُدۡۤ وَٱقۡتَرِب ۩ ١٩ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡